Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 4:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ዘመን በሴ​ሌም፥ ሜት​ሪ​ዳጡ፥ ጣብ​ሄል፥ የቀ​ሩት ተባ​ባ​ሪ​ው​ቻ​ቸ​ውም ለፋ​ርስ ንጉሥ ለአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ጻፉ፤ ደብ​ዳ​ቤ​ውም በሶ​ርያ ፊደ​ልና በሶ​ርያ ቋንቋ ተጽፎ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 በፋርስ ንጉሥ በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፣ ሚትሪዳጡ፣ ጣብኤልና ተባባሪዎቹ ወደ አርጤክስስ ደብዳቤ ጻፉ። ደብዳቤው የተጻፈው በአራማይክ ፊደል፣ በአራማይክ ቋንቋ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፥ ሚትረዳት፥ ጣብኤል ተባባሪዎቹም ወደ ፋርስ ንጉሥ ወደ አርጤክስስ ጻፉ፤ ደብዳቤውም በሶርያ ፊደልና በሶርያ ቋንቋ ተጽፎ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 አርጤክስስ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ሆኖ በተነሣበትም ዘመን፥ እንደገና ቢሽላም፥ ሚትረዳት፥ ጣብኤልና ሌሎቹ የእነርሱ ግብረ አበሮች የክስ ደብዳቤ ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ጻፉባቸው፤ ይህም ደብዳቤ የተጻፈው በሶርያ ፊደልና ቋንቋ ሲሆን ተተርጒሞ በንባብ እንዲሰማ የተላከ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በአርጤክስስም ዘመን ቢሽላም፥ ሚትሪዳጡ፥ ጣብኤልና ተባባሪዎቹ ለፋርስ ንጉሥ ለአርጤክስስ ጻፉ፤ ደብዳቤውም በሶርያ ፊደልና በሶርያ ቋንቋ ተጽፎ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 4:7
12 Referencias Cruzadas  

የኬ​ል​ቅ​ዩም ልጅ ኤል​ያ​ቄም ሳም​ና​ስም ዮአ​ስም ራፋ​ስ​ቂ​ስን፥ “እኛ እን​ሰ​ማ​ለ​ንና በሱ​ር​ስት ቋንቋ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ተና​ገር፤ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥም ቋንቋ አት​ና​ገ​ረን፤ በቅ​ጥ​ርም ላይ ያለው ሕዝብ በሚ​ሰ​ማው ቋንቋ ለምን ትና​ገ​ራ​ለህ?” አሉት።


የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያ​ምም ጠላ​ቶች፥ የም​ር​ኮ​ኞቹ ልጆች ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ እን​ደ​ሚ​ሠሩ ሰሙ።


ንጉ​ሡም ለአ​ዛዡ ለሬ​ሁም፥ ለጸ​ሓ​ፊ​ውም ለሲ​ም​ሳይ፥ በሰ​ማ​ር​ያና በወ​ንዝ ማዶም ለተ​ቀ​መ​ጡ​ትና ለቀ​ሩት ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸው እን​ዲህ የሚ​ለ​ውን መልስ ላከ፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን።


አዛዡ ሬሁም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ሲም​ሳይ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ለን​ጉሡ ለአ​ር​ተ​ሰ​ስታ አንድ የክስ ደብ​ዳቤ ጻፉ።


አዛዡ ሬሁም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ሲም​ሳይ፥ የቀ​ሩ​ትም ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸው፥ ዲና​ው​ያን፥ አፈ​ር​ሳ​ት​ካ​ዋ​ያን፥ ጠር​ፈ​ላ​ው​ያን፥ አፈ​ር​ሳ​ው​ያን፥ አር​ካ​ው​ያን፥ ባቢ​ሎ​ና​ው​ያን፥ ሱስ​ና​ካ​ው​ያን፥ ዴሐ​ው​ያን፥ ኤላ​ማ​ው​ያን፥


በወ​ንዙ ማዶ የነ​በ​ረው ገዥ ተን​ት​ናይ፥ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ፥ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በወ​ንዙ ማዶ የነ​በ​ሩት አፈ​ር​ስ​ካ​ው​ያ​ንም ወደ ንጉሡ ወደ ዳር​ዮስ የላ​ኩት የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነበረ።


ከዚ​ህም ነገር በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መን​ግ​ሥት ዕዝራ የሠ​ራያ ልጅ፥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ፥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ፥


የን​ጉ​ሡ​ንም ትእ​ዛዝ በወ​ንዙ ማዶ ላሉት ለን​ጉሡ ሹሞ​ችና ገዢ​ዎች ሰጡ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝ​ቡ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አከ​በሩ።


በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሃ​ያ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በኔ​ሳን ወር የወ​ይን ጠጅ በፊቱ ነበር፤ ጠጁ​ንም አን​ሥቼ ለን​ጉሡ ሰጠ​ሁት። በፊ​ቱም ሌላ ሰው አል​ነ​በ​ረም።


ኤል​ያ​ቄ​ምና ሳም​ናስ፥ ዮአ​ስም ራፋ​ስ​ቂ​ስን፥ “እኛ እን​ሰ​ማ​ለ​ንና እባ​ክህ፥ በሶ​ርያ ቋንቋ ለባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ ተና​ገር፤ በቅ​ጥ​ርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ አት​ና​ገ​ረን” አሉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos