ዕዝራ 10:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስት ቀንም ሳያልፍ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሃያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በሦስት ቀን ውስጥ የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ በዘጠነኛው ወር በሃያኛውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ስለ ወቅቱ ጕዳይና ስለ ከባዱ ዝናብ በመጨነቅ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀምጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሦስት ቀን ውስጥ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ጥሪ እንደ ተላለፈ በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ በይሁዳና በብንያም ግዛት የሚኖሩት ሁሉ ዘጠነኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው በቤተ መቅደሱ አደባባይ ተሰበሰቡ፤ ሰዎቹ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት በተሰበሰቡበት ጉዳይና በዝናቡ ምክንያት እየተንቀጠቀጡ ቆመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሦስት ቀንም ሳያልፍ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ። |
አሁንም እንደ ጌታዬና የአምላካችንን ትእዛዝ እንደሚፈሩት ምክር፥ ሴቶችን ሁሉ፥ ከእነርሱም የተወለዱትን እንሰድድ ዘንድ ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እናድርግ። ተነሥ እንደ አምላካችንም ትእዛዝ ገሥፃቸው፤ እንደ ሕጉም ያድርጉ፤
“እስከ ሦስት ቀን ድረስ የማይመጣ ሁሉ እንደ ሽማግሎችና እንዳለቆች ምክር ከብቱ ሁሉ ይበዝበዝ፤ እርሱም ከምርኮው ጉባኤ ይለይ” ብሎ ዐዋጅ አስነገረ።
ስለ ምርኮኞቹም መተላለፍ የእስራኤልን አምላክ ቃል የሚፈሩ ሁሉ ወደ እኔ ተሰበሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥዋዕት ድረስ ዐዝኜ ተቀመጥሁ።
እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም።
በላይ በሰማይ ውኆችን ይሰበስባል፤ ከምድርም ዳርቻ ደመናትን ከፍ ያደርጋል፤ ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፤ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።