ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሐዝያ ስለዚህ ነገር ከእኔ ጋር ናቸው፤ ሜሱላምና ሌዋዊው ሰባታይም ይረዱአቸው ነበር።
ዕዝራ 10:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የስደተኞቹም ልጆች እንዲህ አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራ፥ የአባቶችም ቤቶች አለቆች በየአባቶቻቸው ቤቶች ሁሉም በየስማቸው ተለዩ፤ በዐሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ይመረምሩ ዘንድ ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ምርኮኞቹ እንደ ተባለው አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም ከእያንዳንዱ የቤተ ሰብ ምድብ አንዳንድ የቤተ ሰብ ኀላፊ የሆነ ሰው መረጠ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዘገቡ። ከዚያም በዐሥረኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጕዳዩን ለመመርመር ተቀመጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምርኮኞቹም እንዲህ አደረጉ፥ ካህኑ ዕዝራ፥ የአባቶችን መሪዎች መረጠ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች ተለዩ፥ ሁሉም በየስማቸው ተጻፉ፥ በአሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ሊመረምሩ ተቀመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምርኮ የተመለሱት ሁሉ ይህንኑ ዕቅድ ለመቀበል ተስማሙ፤ ስለዚህም ካህኑ ዕዝራ ከጐሣ መሪዎች መካከል መርጦ አስፈጻሚዎችን በመሾም ስም ዝርዝራቸውን መዝግቦ አኖረ፤ እነርሱም ዐሥረኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ጉዳዩን መመርመር ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምርኮኞቹም እንዲህ አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም የአባቶችም ቤቶች አለቆች በየአባቶቻቸው ቤቶች ተለዩ፤ ሁሉም በየስማቸው ተጻፉ፤ በአሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ይመረምሩ ዘንድ ተቀመጡ። |
ነገር ግን የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሐዝያ ስለዚህ ነገር ከእኔ ጋር ናቸው፤ ሜሱላምና ሌዋዊው ሰባታይም ይረዱአቸው ነበር።
እስከ መጀመሪያውም ወር እስከ መጀመሪያው ቀን ድረስ ሠርተው እንግዶቹን ሴቶች ያገቡትን ሰዎች ሁሉ መርምረው ጨረሱ።
ትፈልጋለህ ትመረምራለህም፤ ትጠይቃለህም፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከልህ እንደ ተደረገ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥