“ደግሞም በእግዚአብሔር ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኀጢአታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የእግዚአብሔርም የመቅሠፍቱ ቍጣ በእስራኤል ላይ ነውና” አሉአቸው።
ዕዝራ 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ዕዝራ ተነሥቶ፥ “ተላልፋችኋል፤ የእስራኤልን በደል ታበዙ ዘንድ እንግዶችን ሴቶች አግብታችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ካህኑ ዕዝራ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ታማኞች አልነበራችሁም፤ በእስራኤል በደል ላይ በደል በመጨመር ባዕዳን ሴቶችን አገባችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑ ዕዝራም ተነሣ እንዲህም አላቸው፦ “አልታመናችሁም፥ የእስራኤልን በደል ልታበዙ እንግዶች ሴቶችን አግብታችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ ዕዝራም ቆሞ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “እነሆ እምነታችሁን አጓድላችሁ ተገኝታችኋል፤ ባዕዳን ሴቶችንም በማግባታችሁ ምክንያት በእስራኤል ላይ የበደልን ዕዳ አምጥታችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ዕዝራ ተነሥቶ፦ “ተላልፋችኋል፤ የእስራኤልን በደል ታበዙ ዘንድ እንግዶችን ሴቶች አግብታችኋል። |
“ደግሞም በእግዚአብሔር ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኀጢአታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የእግዚአብሔርም የመቅሠፍቱ ቍጣ በእስራኤል ላይ ነውና” አሉአቸው።
አሁንም የአባቶቻችንን አምላክ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ደስ የሚያሰኘውንም አድርጉ፤ ከምድርም አሕዛብና ከእንግዶች ሴቶች ተለዩ” አላቸው።
ሦስት ቀንም ሳያልፍ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሃያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ።
ትእዛዝህን እናፈርስ ዘንድ ተመልሰናልና፥ ርኵስ ሥራ ከሚሠሩ ከእነዚህ አሕዛብ ጋርም ተጋብተናልና ከእኛ ከሞት የሚያመልጥ እስከማይኖር ድረስ ፈጽመህ አትቈጣን።
እንዲህም አልሁ፥ “አምላኬ ሆይ፥ ኀጢአታችን በራሳችን ላይ በዝቶአልና፥ በደላችንም ወደ ሰማይ ከፍ ብሎአልና አምላኬ ሆይ፥ ፊቴን ወደ አንተ አነሣ ዘንድ አፍራለሁ፤ እፈራማለሁ።
እነሆም፥ የእግዚአብሔርን መዓት በእስራኤል ላይ አብዝታችሁ ትጨምሩ ዘንድ እናንተ በኀጢአተኞች ሰዎች በደል በአባቶቻችሁ ፋንታ ተነሥታችኋል።