Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 28:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “ደግ​ሞም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በእኛ ላይ በደል ታመ​ጡ​ብ​ና​ላ​ች​ሁና፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንና በደ​ላ​ች​ንን ታበ​ዙ​ብ​ና​ላ​ች​ሁና የተ​ማ​ረ​ኩ​ትን ወደ​ዚህ አታ​ግቡ፤ በደ​ላ​ችን ታላቅ ነውና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ቍጣ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ነውና” አሉ​አ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “እነዚህን ምርኮኞች እዚህ ማምጣት አልነበረባችሁም፤ አለዚያ እኛ በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች እንሆናለን፤ በኀጢአታችንና በበደላችን ላይ ሌላ ልትጨምሩ ታስባላችሁን? በደላችንማ ቀድሞውኑ በዝቷል፤ ቍጣውም በእስራኤል ላይ ነውና” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነርሱም እንዲህ አሉአቸው፦ “በጌታ ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኃጢአታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የመቅሰፍቱም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነውና።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እንዲህም አሉአቸው፦ “እነዚህን እስረኞች ወደዚህ አታምጡብን! ከዚህ ቀደም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን ስላሳዘንን ቊጣው በእኛ ላይ ወርዶአል፤ አሁንም በበደል ላይ በደል እንድንፈጽም ትፈልጋላችሁን?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ደግሞም “በእግዚአብሔር ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኃጢያታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የመቅሰፍቱም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነውና” አሉአቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 28:13
9 Referencias Cruzadas  

የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ትተው ባዕድ አም​ላ​ክ​ንና ጣዖ​ታ​ትን አመ​ለኩ፤ በዚ​ያም ወራት በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ቍጣ ወረደ።


ደግ​ሞም ከኤ​ፍ​ሬም ልጆች አለ​ቆች የአ​ናን ልጅ ዓዛ​ር​ያስ፥ የመ​ስ​ለ​ሞት ልጅ በራ​ክያ፥ የሳ​ሎም ልጅ ሕዝ​ቅ​ያስ፥ የአ​ዳሊ ልጅ አማ​ስያ ከሰ​ልፍ የተ​መ​ለ​ሱ​ትን ተቃ​ወ​ሙ​አ​ቸው።


ሰል​ፈ​ኞ​ቹም ምር​ኮ​ኞ​ቹ​ንና ምር​ኮ​ውን በአ​ለ​ቆ​ችና በጉ​ባኤ ሁሉ ፊት ተዉ።


እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መዓት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አብ​ዝ​ታ​ችሁ ትጨ​ምሩ ዘንድ እና​ንተ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች በደል በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፋንታ ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል።


እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ።


ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችኋል።


ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።


በገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ደረሱ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩ​አ​ቸው


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos