ሕዝቅኤል 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተም ስንዴንና ገብስን፥ አተርንና ባቄላን፥ ምስርንና አጃን ወደ አንተ ውሰድ፤ በአንድ ዕቃም ውስጥ አድርገህ እንጀራ ጋግር፤ በጎንህ እንደ ተኛህባት ቀን ቍጥር ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ትበላዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስንዴና ገብስ፣ ባቄላና ምስር እንዲሁም ዘንጋዳና አጃ ወስደህ በአንድ ሸክላ ውስጥ አስቀምጥ፤ ከዚያም ለራስህ እንጀራ ጋግር፤ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን በጐንህ በምትተኛበት ጊዜ ትመገበዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም ለራስህ ስንዴና ገብስ፥ ባቄላና ምስር፥ ማሽላና አጃን ውሰድ፥ በአንድ ዕቃ ውስጥ አድርጋቸው፥ ለራስህም ምግብ አዘጋጅ፥ በጎንህ እንደ ምትተኛበት ቀን ቍጥር ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ትበላዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሁንም ስንዴና ገብስ፥ ባቄላና ምስር፥ ማሽላና ጠመዥ ውሰድ፤ ሁሉንም በአንድነት ደባልቀህ እንጀራ ጋግር፤ ይህም በግራ ጐንህ በምትተኛባቸው በ 390 ቀኖች ውስጥ የምትመገበው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ስንዴንና ገብስን ባቄላንና ምስርን ጤፍንና አጃን ወደ አንተ ውሰድ፥ በአንድ ዕቃም ውስጥ አድርገህ እንጀራ ጋግር፥ በጐድንህ እንደ ተኛህበት ቀን ቍጥር ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ትበላዋለህ። |
እርሻውን ባስተካከለ ጊዜ ጥቂት ጥቍሩን አዝሙድ፥ ከሙኑንም፥ ዳግመኛም ስንዴውን፥ ገብሱንም፥ አጃውንም በየስፍራው የሚዘራ አይደለምን?
እግዚአብሔርም፥ “እንዲሁ የእስራኤል ልጆች እነርሱን በምበትንባቸው በአሕዛብ መካከል ንጹሕ ያልሆነ እንጀራቸውን ይበላሉ” አለ።
ደግሞም እንዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የኢየሩሳሌምን እንጀራ በትር እሰብራለሁ፤ በችግር እያሉ እንጀራን በሚዛን ይበላሉ፥ እየደነገጡም ውኃን በልክ ይጠጣሉ፤