የእግዚአብሔርንም ቤት በየአደባባዩና በየመጋረጃው ውስጥ ለማገልገል፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ለማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት ለመሥራት ከአሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞአቸው ነበር።
ዘፀአት 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴ እንደ አለ አደረገ፤ ጓጕንቸሮቹም ከቤት፥ ከመንደርም፥ ከሜዳም ሞቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፤ ጓጕንቸሮቹም በየቤቱ ውስጥ፣ በየዐጥር ግቢውና በየሜዳው ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘረጋ፥ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታ፥ በሰውና በእንስሳም ላይ ተናካሽ ትንኝ ሆነ፤ በግብጽ ምድር ያለ የምድር ትቢያ ሁሉ ተናካሽ ትንኝ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ በጸለየውም መሠረት እግዚአብሔር በየቤቱ፥ በየቅጽር ግቢውና በየመስኩ ያሉት ጓጒንቸሮች ሁሉ ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴ እንዳለ አደረገ፤ ጓጕንቸሮቹም ከቤት ከወጀድም ከሜዳም ሞቱ። |
የእግዚአብሔርንም ቤት በየአደባባዩና በየመጋረጃው ውስጥ ለማገልገል፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ለማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት ለመሥራት ከአሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞአቸው ነበር።
ጓጕንቸሮቹም ከአንተ፥ ከቤቶችህም፥ ከመንደሮችህም፥ ከሹሞችህም፥ ከሕዝብህም ይሄዳሉ፤ በወንዙም ብቻ ይቀራሉ” አለው።