ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “የሦስት ዓመት ራብ በሀገርህ ላይ ይምጣብህን? ወይስ ጠላቶችህ እያሳደዱህ ሦስት ወር ከእነርሱ ትሸሽን? ወይስ የሦስት ቀን ቸነፈር በሀገርህ ላይ ይሁን? የሚሻልህን ምረጥ። አሁንም ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስብና መርምር” ብሎ ነገረው።
ዘፀአት 7:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈጸመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አባይን ከመታ ሰባት ቀን ሞላ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈጸመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን አለፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈጸመ። |
ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “የሦስት ዓመት ራብ በሀገርህ ላይ ይምጣብህን? ወይስ ጠላቶችህ እያሳደዱህ ሦስት ወር ከእነርሱ ትሸሽን? ወይስ የሦስት ቀን ቸነፈር በሀገርህ ላይ ይሁን? የሚሻልህን ምረጥ። አሁንም ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስብና መርምር” ብሎ ነገረው።
ማንም ወንድሙን አላየም፤ ሦስት ቀን ሙሉም ከመኝታው ማንም አልተነሣም፤ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ሁሉ ብርሃን ነበራቸው።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።