ዘፀአት 40:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወርቁንም ማዕጠንት በምስክሩ ታቦት ፊት ታኖራለህ፤ በድንኳኑም ደጃፍ ፊት መጋረጃውን ትጋርዳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዕጣኑን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት አስቀምጠው፤ ከማደሪያውም መግቢያ ላይ መጋረጃውን አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዕጣን የሚሆነውን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ፊት ታኖራለህ፥ በማደሪያውም ደጃፍ መጋረጃውን ትጋርዳለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕጣን የሚቃጠልበትን የወርቅ መሠዊያ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት አቁመው፤ በድንኳኑም መግቢያ ደጃፍ መጋረጃውን ስቀል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዕጣንም የሚሆነውን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ፊት ታኖራለህ፥ በማደሪያውም ደጃፍ ፊት መጋረጃውን ትጋርዳለህ። |
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሠራች የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ፥ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።