ዘፀአት 40:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኅብስተ ገጹንም በላዩ በእግዚአብሔር ፊት አሰናዳ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ኅብስቱን በላዩ ላይ በእግዚአብሔር ፊት አኖረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ኅብስቱን በላዩ በጌታ ፊት አሰናዳ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን የተቀደሰ ኅብስት በገበታው ላይ አሰናዳ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንጀራውን በላዩ በእግዚአብሔር ፊት አሰናዳ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው መቅረዙን በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ በገበታውም ፊት ለፊት፥ በድንኳኑ በአዜብ በኩል አኖረ፤
“የስንዴ ዱቄት ወስደህ ዐሥራ ሁለት ኅብስት ጋግር፤ በእያንዳንዱ ኅብስት ውስጥ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ይሁን።
የመጀመሪያዪቱም ድንኳን ተዘጋጅታ ነበርና፥ በእርስዋም ቅድስት በምትባለው ውስጥ መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት ነበረባት።