እኔም መልሼ፥ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛም ንጹሓን ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ዕድል ፋንታና መብት፥ መታሰቢያም የላችሁም” አልኋቸው።
ዘፀአት 39:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእስራኤልም ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች ይሆኑ ዘንድ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፥ በልብሰ መትከፉ ጫንቃዎች ላይ አደረጓቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው በኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ ለእስራኤል ልጆች እንደ መታሰቢያ ድንጋዮች አያያዟቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ለእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች እንዲሆኑ በኤፉዱ በትከሻው ላይ አደረጋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ነገድ በመወከል እንዲታሰቡ በትከሻ ላይ በሚወርዱት በኤፉዱ ጥብጣቦች ላይ አኖሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች ይሆኑ ዘንድ በኤፉዱ ጫንቃዎች ላይ አደረጋቸው። |
እኔም መልሼ፥ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፤ እኛም ንጹሓን ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ዕድል ፋንታና መብት፥ መታሰቢያም የላችሁም” አልኋቸው።
ለእስራኤል ልጆችም የመታሰቢያ ድንጋዮች ይሆኑ ዘንድ ሁለቱን ዕንቍዎች በልብሰ መትከፉ ጫንቃዎች ላይ ታደርጋለህ፤ አሮንም በሁለቱ ጫንቃዎች ላይ ለመታሰቢያ ስማቸውን በእግዚአብሔር ፊት ይሸከማል።
አሮንም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ለዘለዓለም መታሰቢያ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርዱ ልብሰ እንግድዓ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸከም።
እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ወንጌል በዓለሙ ሁሉ በሚሰበክበት በማናቸውም ስፍራ፥ እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ ሊሆን ይነገራል።”
አንተ በምድር ሁሉ ጌታ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ስንሻገር የዮርዳኖስ ወንዝ ስለ ደረቀ ነው፤ እነዚህ ድንጋዮችም ለእስራኤል ልጆች ለዘለዓለም መታሰቢያ ይሆናሉ።”