የእግር መታጠቢያዎችን፥ የእጅ መታጠቢያዎችን፥ ጋኖችን፥ የሥጋ ማውጫ ሜንጦዎችንና ኪራም የሠራውን ሥራ ሁሉ ከንጹሕ ናስ ሠርቶ ለንጉሡ ለሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት አቀረበለት።
ዘፀአት 38:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ ምንቸቶቹንም፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ሜንጦዎቹንም፥ የእሳት ማንደጃዎቹንም አደረገ፤ ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕቃዎቹንም ሁሉ ይኸውም ምንቸቶቹን፣ መጫሪያዎቹን፣ መርጫ ጐድጓዳ ሳሕኖቹን፣ ሜንጦዎቹንና የእሳት መያዣዎቹን ከንሓስ ሠሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ፥ ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖቹን፥ ሜንጦቹን፥ ማንደጃዎቹን ሠራ፤ ዕቃዎቹን በሙሉ ከነሐስ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመሠዊያው ላይ ያሉትንም የመገልገያ ዕቃዎች፥ ድስቶችንም፥ የእሳት መጫሪያዎቹንም፥ ጐድጓዳ ሳሕኖችንም፥ ሜንጦዎቹንም፥ ማንደጃዎቹንም ከነሐስ ሠራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ ምንቸቶቹንም፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ሜንጦቹንም፥ ማንደጃዎቹንም አደረገ፤ ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አደረገ። |
የእግር መታጠቢያዎችን፥ የእጅ መታጠቢያዎችን፥ ጋኖችን፥ የሥጋ ማውጫ ሜንጦዎችንና ኪራም የሠራውን ሥራ ሁሉ ከንጹሕ ናስ ሠርቶ ለንጉሡ ለሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት አቀረበለት።
ለመሠዊያው ክዳን ሥራለት፤ መሸፈኛውን፥ ጽዋዎቹን፥ የሥጋ ሜንጦዎቹን፥ የእሳት መጫሪያዎቹንም አድርግ። ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አድርግ።
እንደ መረብ ሆኖም የተሠራ የናስ መከታ ለመሠዊያው አደረገ፤ መከታውም እስከ መሠዊያው እኩሌታ ይደርስ ዘንድ በመሠዊያው በሚዞረው በደረጃው ታች አደረገው።
መሥዋዕት በሚሠዉ በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ የነበረ የካህኑንም ሕግ አያውቁም ነበረ፤ ሕዝቡም ሁሉ መሥዋዕት በሠዉ ጊዜ የካህኑ ብላቴና ይመጣ ነበር፤ በእጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበር፤