በስተጐኑ ስድስት ቅርንጫፎች ይውጡለት፤ ሦስት የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስትም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ይውጡ።
ዘፀአት 37:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስተጎንዋ ስድስት ቅርንጫፎች ወጡላት፤ ሦስቱ የመቅረዝዋ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስቱም የመቅረዝዋ ቅርንጫፎች በሁለተኛው ወገን ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስቱ በአንድ በኩል ሦስቱ በሌላ በኩል በመሆን ስድስት ቅርንጫፎች ከመቅረዙ ጐኖች ተሠርተው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጎኑም ስድስት ቅርንጫፎች ወጡለት፤ ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ በኩል፥ ሦስቱም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ በኩል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንድ በኩል ሦስት፥ በሌላ በኩል ሦስት በመሆን ከጐኖቹ ስድስት ቅርንጫፎች እንዲወጡ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስተጎኑም ስድስት ቅርንጫፎች ወጡለት፤ ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስቱም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ወጡ። |
በስተጐኑ ስድስት ቅርንጫፎች ይውጡለት፤ ሦስት የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስትም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ይውጡ።
መቅረዝዋንም ከጥሩ ወርቅ አደረገ፤ መቅረዝዋንም ከእግርዋና ከአገዳዋ ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ፤ ጽዋዎችዋን፥ ጕብጕቦችዋን፥ አበቦችዋን ከዚያው በአንድነት አደረገ።
በአንደኛው ቅርንጫፍ ጕብጕቡንና አበባውን፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕቡንና አበባውን፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ እንዲሁም ከመቅረዝዋ ለወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አደረገ።