ዘፀአት 36:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳንቆቹንም በወርቅ ለበጡአቸው፤ ቀለበቶቻቸውንም የመወርወሪያ ቤት እንዲሆኑላቸው ከወርቅ አደረጉ፤ መወርወሪያዎቹንም በወርቅ ለበጡአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወጋግራዎቹን በወርቅ ለበጧቸው፤ አግዳሚዎቹን ለመያዝም የወርቅ ቀለበቶችን ሠሩ፤ እንዲሁም አግዳሚዎቹን በወርቅ ለበጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳንቃዎቹን በወርቅ ለበጣቸው፥ ቀለበቶቻቸውንም የመወርወሪያው ማስገቢያ እንዲሆኑ ከወርቅ ሠራ፥ መወርወሪያዎቹንም በወርቅ ለበጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተራዳዎቹንም በወርቅ ለበጡአቸው፤ ዋልታዎቻቸውንም የመወርወሪያው መተላለፊያ ይሆኑ ዘንድ ከወርቅ ሠሩ፤ መወርወሪያዎቹም በወርቅ የተለበጡ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳንቆቹንም በወርቅ ለበጡአቸው፤ ቀለበቶቻቸውንም የመወርወሪያ ቤት እንዲሆኑላቸው ከወርቅ አደረጉ፤ መወርወሪያዎቹንም በወርቅ ለበጡአቸው። |
መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊ፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ አደረጉ፤ ኪሩቤልንም በጥልፍ ሥራ በእርሱ ላይ አደረጉ።