ዘፀአት 30:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርጉድም አምስት መቶ ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን፥ የወይራ ዘይትም አንድ የኢን መስፈሪያ ትወስዳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምስት መቶ ሰቅል ብርጕድ ውሰድ፤ ሁሉም እንደ መቅደሱ ሰቅልና አንድ የሂን መስፈሪያ የወይራ ዘይት ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርጉድ አምስት መቶ ሰቅል በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት፥ አንድ የኢን መሥፈሪያ የወይራ ዘይት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስድስት ኪሎ ግራም ብርጒድ ውሰድ ይህም ሁሉ በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ ይሁን፤ በዚህም ላይ አራት ሊትር ዘይት ጨምርበትና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርጕድም አምስት መቶ ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን፥ የወይራ ዘይትም አንድ የኢን መሥፈሪያ ትወስዳለህ። |
ከአንዱ ጠቦትም ጋር የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመጠጥ ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ።
“አንተም ክቡሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተመረጠ የከርቤ አበባ አምስት መቶ ሰቅል፥ የዚህም ግማሽ ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤ ያማረ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤
የእውነትም ሚዛን፥ የእውነትም መመዘኛ፥ የእውነትም የፈሳሽ መስፈሪያ ይሁንላችሁ፤ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ ነኝ።
ለመጠጥ ቍርባንም የኢን መስፈሪያ የሆነ መልካም ዱቄት አራተኛ እጅ በሚቃጠለው መሥዋዕት ወይም በእህሉ ቍርባን ላይ ያደርጋል፤ ለእያንዳንዱ ጠቦት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥዋዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድርግ።