ይቈጠሩ ዘንድ የሚያልፉት ሁሉ የሚሰጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ይሰጣል። ሰቅሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰቅሉም ግማሽ ለእግዚአብሔር ቍርባን ነው።
ዘፀአት 30:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይቈጠር ዘንድ የሚያልፈው ሁሉ፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም ከፍ ያለ፥ የእግዚአብሔርን ስጦታ ይሰጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከሃያ በላይ ሆኖ ወደ ተቈጠሩት ያለፉት ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማቅረብ አለባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ቆጠራ የሚያልፍ፥ ሃያ ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ ይህንን ስጦታ ለጌታ ይስጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሕዝብ ቈጠራው ለመግባት ዕድሜው የፈቀደለት፥ ማለትም ኻያ ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር መባ ያቅርብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰቅሉ ሀያ ኦቦሊ ነው። አልፎ የተቆጠረ ሁሉ፥ ከሀያ አመት ጀምሮ ከዚያም ከፍ ያለ፥ የእግዚአብሔርን ስጦታ ይሰጣል። |
ይቈጠሩ ዘንድ የሚያልፉት ሁሉ የሚሰጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ይሰጣል። ሰቅሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰቅሉም ግማሽ ለእግዚአብሔር ቍርባን ነው።
በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበሩን ሁሉ ሰበሰቡአቸው፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ወንድ ሁሉ በየራሱ፥ በየወገኑም፥ በየአባቶቻቸውም ቤቶች፥ በየስማቸው ቍጥር ትውልዳቸውን ተናገሩ።
የእስራኤል በኵር የሮቤል ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥
ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን፥ ከእስራኤል ወደ ሰልፍ የሚወጡትን ሁሉ፥ አንተና አሮን በየሠራዊቶቻቸው ቍጠሩአቸው።
በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ፤ የተቈጠራችሁ ሁሉ፥ እንደ ቍጥራችሁ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እናንተ ያጕረመረማችሁብኝ፥
“ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን፥ ከእስራኤል ወደ ሰልፍ የሚወጣውን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤት ቍጠሩ።”
ከግብፅ የወጡት ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት መልካምንና ክፉን የሚያውቁ ሰዎች እኔን ፈጽመው አልተከተሉምና ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እሰጥ ዘንድ የማልሁባትን ምድር አያዩም፤