ዘፀአት 3:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤቷ፥ በቤቷም ካለችው ሴት የብር ዕቃ፥ የወርቅ ዕቃ፥ ልብስም ትዋሳለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይም ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዷ ዕብራዊት ከጎረቤቷም ይሁን ዐብራት ከምትኖረው ግብጻዊት የብርና የወርቅ ጌጣጌጦች እንደዚሁም ልብስ እንድትሰጣት ትጠይቅ። እነዚህንም ሁሉ ወስዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ታስጌጧቸዋላችሁ፤ ታለብሷቸዋላችሁም። በዚህም መንገድ የግብጻውያኑን ሀብት በእጃችሁ አግብታችሁ ትወጣላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር እቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዕብራውያን ሴቶች እያንዳንዳቸው ጐረቤት በመሆን አብረዋቸው የሚኖሩትን ግብጻውያን ሴቶች ወርቅ፥ ብርና፥ ጌጣጌጥና ልብስ እንዲሰጡአቸው ይጠይቃሉ፤ ይህንንም ሁሉ ወስዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ታለብሳላችሁ፤ በዚህም ዐይነት ግብጻውያንን በዝብዛችሁ ትወጣላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር ዕቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።” |
ለሚያዋርዱአችሁ ወዮላቸው! እናንተን ግን የሚያዋርዳችሁ የለም፤ የሚወነጅላችሁ እናንተን የሚወነጅል አይደለም፤ ወንጀለኞች ይጠመዳሉ፤ ይያዛሉም፤ ብል እንደበላው ልብስም ያልቃሉ።
እንጨትን ከሜዳ አይወስዱም፤ ከዱርም አይቈርጡም፤ ነገር ግን የጦር መሣሪያን በእሳት ያነድዳሉ፤ የገፈፉአቸውንም ይገፍፋሉ፤ የበዘበዙአቸውንም ይበዘብዛሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።