ዘፀአት 26:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶዎች ከማይነቅዝ ዕንጨት አድርግ፤ በወርቅም ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ አምስትም የናስ እግሮች አድርግላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዚህም መጋረጃ የወርቅ ኵላቦችንና ከግራር ዕንጨት የተሠሩ፣ በወርቅ የተለበጡ ዐምስት ምሰሶዎችን አብጅ፤ ዐምስት የንሓስ መቆሚያዎችንም አብጅላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶች ከግራር እንጨት አድርግ፤ በወርቅም ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ አምስትም እግሮች አድርግላቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶዎችን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ ለእነዚህ ምሰሶዎች ከነሐስ የተሠሩ አምስት እግሮች አብጅላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶች ከግራር እንጨት አድርግ፥ በወርቅም ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ አምስትም እግሮች አድርግላቸው። |
አምስቱንም ምሰሶዎች፥ ኵላቦቻቸውንም አደረጉ፤ ጉልላቶቻቸውንና ዘንጎቻቸውንም በወርቅ ለበጡአቸው፤ አምስቱም እግሮቻቸው የናስ ነበሩ።
ከእርሱም የምስክሩን ድንኳን ደጃፍ እግሮች፥ የናሱንም መሠዊያ፥ ለእርሱም የሆነውን የናሱን መከታ፥ የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥