ዘፀአት 26:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእያንዳንዱም ሳንቃ ርዝመቱ ዐሥር ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱም ወጋግራ ርዝመቱ ዐሥር ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳንቃውም ሁሉ ርዝመቱ ዐሥር ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ ተራዳ ርዝመቱ አራት ሜትር፥ የጐኑም ስፋት ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳንቃውም ሁሉ ርዝመቱ አሥር ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን። |
ለእያንዳንዱም ሳንቃ አንዱን በአንዱ ላይ የሚያያይዙ ሁለት ማጋጠሚያዎች ይሁኑለት፤ ለድንኳኑ ሳንቆች ሁሉ እንዲሁ አድርግ።