“ለድንኳኑም ሳንቆችን ከማይነቅዝ ዕንጨት አድርግ።
“ለማደሪያው ድንኳን ከግራር ዕንጨት ወጋግራዎችን አብጅ።
“ለማደሪያውም የሚቆሙትን ሳንቃዎች ከግራር እንጨት አድርግ።
“ድንኳኑን የሚደግፉ ቋሚ ተራዳዎች ከግራር እንጨት ሥራ።
ለማደሪያውም የሚቆሙትን ሳንቆች ከግራር እንጨት አድርግ።
የፍየልም ጠጕር፥ ቀይ የተለፋ የአውራ በግ ቍርበት፥ ሰማያዊ ቀለም የገባ ቍርበት፥ የማይነቅዝ ዕንጨት፥
የእያንዳንዱም ሳንቃ ርዝመቱ ዐሥር ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።
ለድንኳኑም በደቡብ በኩል ሃያ ሳንቆችን አድርግ።