“መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ፤ የመቅረዙም እግሩና ቅርንጫፎቹ የተቀጠቀጠ ሥራ ይሁን፤ ጽዋዎቹም፥ ጕብጕቦቹም፥ አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት።
ዘፀአት 25:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመቅረዙም ጕብጕቦቹንና አበቦቹን፥ አራትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች ከእርሱ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመቅረዙም ላይ አበባዎች እንቡጥና ቀንበጥ ያሏቸው አራት የለውዝ አበባ ቅርጽ ያሏቸው ጽዋዎች ይኑሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅረዙም እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ አራት ጽዋዎች ይኑሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመቅረዙም ዘንግ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስል አራት የአበባ ወርድ ጌጥ ያለው ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅረዙም ጕብጕቦቹንና አበቦቹን አራትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች አድርግ። |
“መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ፤ የመቅረዙም እግሩና ቅርንጫፎቹ የተቀጠቀጠ ሥራ ይሁን፤ ጽዋዎቹም፥ ጕብጕቦቹም፥ አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት።