ዘፀአት 23:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊትህም ተርብ እሰድዳለሁ፤ አሞራዊውንም፥ ኤዌዎያዊውንም፥ ከነዓናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም ከፊትህ ያባርራቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤዊያውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጢያውያንን ከመንገድህ ለማስወጣት ተርብን በፊትህ እሰድዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊትህም ተርብ እሰድዳለሁ፥ ኤዊያዊውንም ከነዓናዊውንም ኬጢያዊውንም ከፊትህ አባርራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጠላቶችህ ላይ ሽብር እልክባቸዋለሁ። አንተም ወደ ፊት ስትሄድ ሒዋውያንን፥ ከነዓናውያንንና ሒታውያንን ከፊትህ አባርራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊትህም ተርብ እሰድዳለሁ፥ ኤዊያዊውንም ከነዓናዊውንም ኬጢያዊውንም ከፊትህ አባርራለሁ። |
መልአኬንም ከአንተ ጋር በፊትህ እልካለሁ፤ ከነዓናዊውን፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውን፥ ኤዌዎናውዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ያወጣቸዋል።
በዚህ ቀን የማዝዝህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ፥ እኔ አሞሬዎናዊውን፥ ከነዓናዊውንም፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ከፊትህ አወጣለሁ።