እርሱም አለ፥ “አሁንም እንዲሁ እንደ ነገራችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ አገልጋይ ይሁነኝ፤ እናንተም ንጹሓን ትሆናላችሁ።”
ዘፀአት 22:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀሐይ ግን ከወጣችበት የደም ዕዳ አለበት፤ የገደለው ይገደል፤ ሌባው ቢያዝ የሚከፍለውም ቢያጣ ስለ ሰረቀው ይሸጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ፀሓይ ከወጣች በኋላ ከተፈጸመ፣ ሰውየው በነፍስ ግድያ ይጠየቃል። “ሌባ የሰረቀውን መክፈል አለበት፤ ምንም ከሌለው ግን የሰረቀውን ይከፍል ዘንድ ይሸጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰረቀው በሬ ወይም አህያ ወይም በግ ቢሆንና በሕይወት ሳለ በእጁ ቢገኝ፥ የሰረቀውን ሁለት እጥፍ አድርጎ ይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀሐይ ግን ከወጣችበት የደም ዕዳ አለበት፤ ሌባው የሰረቀውን ይመልስ፤ የሚከፍለውም ቢያጣ ስለ ሰረቀው ይሸጥ። |
እርሱም አለ፥ “አሁንም እንዲሁ እንደ ነገራችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ አገልጋይ ይሁነኝ፤ እናንተም ንጹሓን ትሆናላችሁ።”
ካህናት ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ወደ ልቧ የሚገባ ነገርን ተናገሩ፤ ውርደቷ እንደ ተፈጸመ፥ ኀጢአቷም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች አጽናኑአት።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ተቈጣ፤ ወደ ማረኳቸውም ማራኪዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ማረኩአቸውም፤ በዙሪያቸውም ባሉት በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ከዚያም ወዲያ ጠላቶቻቸውን ሊቋቋሙ አልቻሉም።