ዘፀአት 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በአንድ በሬ ፋንታ አምስት በሬዎች፥ በአንድ በግም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው በሬ ወይም በግ ሰርቆ ቢያርድ ወይም ቢሸጥ በአንድ በሬ ምትክ ዐምስት በሬዎች፤ በአንድ በግ ምትክ አራት በጎች ይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሌባ ቤት ሲሰብር ቢገኝ፥ ቢመታና ቢሞት፥ በመታው ሰው ላይ ደሙ የለበትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው አንድ በሬ ወይም አንድ በግ ሰርቆ ቢያርድ ወይም ቢሸጥ ስለ አንድ በሬ አምስት በሬዎች፥ ስለ አንድ በግ አራት በጎች ይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በበሬው ፈንታ አምስት በሬዎች፥ በበጉም ፈንታ አራት በጎች ይክፈል። |
በሬውም ትናንትና ከትናንት ወዲያ ተዋጊ መሆኑ ቢታወቅ ለባለቤቱም ቢመሰክሩለት፥ ባለቤቱም ባያስወግደው በሬውን በበሬው ፋንታ ይስጥ፤ የሞተውም ለእርሱ ይሁነው።
በእጆችሽም የንጹሓን ድሆች ደም ተገኝቶአል፤ በዛፍ ሁሉ ላይ በግልጥ አገኘሁት እንጂ በጕድጓድ ፈልጌ አላገኘሁትም።
ኀጢአተኛውም መያዣን ቢመልስ፥ የነጠቀውንም ቢከፍል፥ በሕይወትም ትእዛዝ ቢሄድ፥ ኀጢአትም ባይሠራ፥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።
ያች ሰውነት ብትናዘዝ፥ ያደረገችውንም ኀጢአት ሁሉ ብትናገር የወሰደውን ዓይነቱን ሁሉ ይመልስ። አምስተኛ እጅም ለባለ ገንዘቡ ይጨምር።
ዘኬዎስም ቆመና ጌታችንን እንዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገንዘቤን እኩሌታ ለነዳያን እሰጣለሁ፤ የበደልሁትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከፍለዋለሁ።”