“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።
ዘፀአት 21:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእስራኤል ልጆች አንዱን የሰረቀ ወይም ግፍ የፈጸመበት፥ ወይም አሳልፎ ቢሰጠው፥ ወይም በእርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ እርሱ ይገደል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ይገደል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቱን ወይም እናቱን የሚያዋርድ ፈጽሞ ይሙት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ በሞት ይቀጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል። |
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።
“ሁለት ሰዎችም እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ አንዱም ሌላውን በድንጋይ ወይም በጡጫ ቢመታ፥ ያም ባይሞት ነገር ግን በአልጋው ላይ ቢተኛ፥
የከተማዉም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ደብድበው ይግደሉት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፤ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።