ዘፀአት 15:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ጦርነትን ያጠፋል፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ተዋጊ ነው፥ ስሙም ጌታ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ብርቱ ጦረኛ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው፤ |
የሰረገሎቹንም መንኰራኵር አሰረ፤ ወደ ጭንቅም አገባቸው፤ ግብፃውያንም፥ “እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።
ሙሴም እግዚአብሔርን፥ “እነሆ፥ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች እሄዳለሁ፤ የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ እላቸዋለሁ፤ ‘ስሙስ ማን ነው?’ ብለው በጠየቁኝ ጊዜ ምን እላቸዋለሁ?” አለው።
እግዚአብሔርም ለሙሴ ነገረው፤ እንዲህ ሲል፥ “ያለና የሚኖር እኔ ነኝ፤ እንዲህ ለእስራኤል ‘ያለና የሚኖር’ ወደ እናንተ ላከኝ ትላቸዋለህ” አለው።
ዳግመኛም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፥ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ፦ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘለዓለም ስሜ ነው፤ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይወጣል፤ ኀይለኛውንም ያጠፋል፤ ቅንአትንም ያስነሣል፤ በጠላቶቹም ላይ በኀይል ይጮኻል።