ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በዙሪያ መንገድ በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች በአምስተኛው ትውልድ ከግብፅ ምድር ወጡ።
ዘፀአት 14:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግብፃውያንም፥ የፈርዖን ፈረሶች፥ ሰረገሎቹም፥ ፈረሰኞቹም፥ ሠራዊቱም ሁሉ አሳደዱአቸው፤ በባሕሩ ዳር በብኤልሴፎን ፊት ለፊት ባለው ገላጣ መንደር አንጻርም ሰፍረው አገኙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግብጻውያን፣ ይኸውም የፈርዖን ፈረሶችና ሠረገላዎች፣ ፈረሰኞችና እግረኞች ሁሉ እስራኤላውያንን አሳደዷቸው፤ በበኣልዛፎን አንጻር በባሕሩ አጠገብ በፊሀሒሮት ሰፍረው ሳሉ ደረሱባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግብፃውያንም የፈርዖን ፈረሶችና ሰረገሎች ፈረሰኞቹም ሠራዊቱም ሁሉ፥ አሳደዱአቸው፤ በባሕሩ በበዓልጽፎን ፊት ለፊት ባለው በፒሃሒሮት ሰፍረው አገኙአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብጽ ሠራዊት በፈረሶችና በሠረገላዎች ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ ተከታተላቸው፤ በቀይ ባሕር ፊት ለፊት ባሉት በፒሃሒሮት በባዓልጸፎን አጠገብ በሰፈሩበት ቦታ ደረሱባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግብፃውያንም የፈርዖን ፈረሶች ሰረገሎቹም ፈረሰኞቹም ሠራዊቱም ሁሉ፥ አሳደዱአቸው፤ በባሕሩ ዳር በበኣልዛፎን ፊት ለፊት ባለው በፊሀሒሮት አጠገብ ሰፍረው አገኙአቸው። |
ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በዙሪያ መንገድ በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች በአምስተኛው ትውልድ ከግብፅ ምድር ወጡ።
“ተመልሰው በመግደሎና በባሕር መካከል፥ በብኤልሴፎን ፊት ለፊት ባለው ገላጣ መንደር አንጻር እንዲሰፍሩ ለእስራኤል ልጆች ተናገር፤ ከእርሱም አጠገብ በባሕር ዳር ትሰፍራላችሁ።
ጠላትም፦ ‘አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፤ ምርኮም እካፈላለሁ፤ ነፍሴንም አጠግባታለሁ፤ በሰይፌም እገድላለሁ፤ በእጄም እገዛለሁ’ አለ።
ከዚያም በኋላ አባቶቻችሁን ከግብፅ አወጣኋቸው፤ ወደ ባሕሩም ገባችሁ፤ ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሶች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ ተከተሉአቸው።