ዘፀአት 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን፦ ‘ከግብፅ በወጣሁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ስለአደረገልኝ ነው’ ስትል ለልጅህ ትነግረዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያችም ዕለት፣ ‘እኔ ይህን የማደርገው ከግብጽ ምድር በወጣሁበት ጊዜ እግዚአብሔር ስላደረገልኝ ነገር ነው’ ብለህ ለልጅህ ንገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን፦ “ከግብጽ በወጣሁ ጊዜ ጌታ ስላደረገልኝ ነው” ስትል ለልጅህ ትነግረዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓሉም በሚከበርበት ጊዜ ይህን ሁሉ የምታደርጉት ከግብጽ በወጣችሁበት ጊዜ እግዚአብሔር ያደረገላችሁን መልካም ነገር ሁሉ ለማስታወስ መሆኑን ለልጆቻችሁ ተርኩላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን፦ ‘ከግብፅ በወጣሁ ጊዜ እግዚአብሔር ስላደረገልኝ ነው’ ስትል ለልጅህ ትነግረዋለህ። |
በግብፃውያንም ላይ የተዘባበትሁትን ሁሉ፥ ያደረግሁባቸውንም ተአምራቴን በልጆቻችሁና በልጅ ልጆቻችሁ ጆሮች ትነግሩ ዘንድ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
እንዲህም ይሆናል፤ ከዚህ በኋላ ልጅህ፦ ‘ይህ ምንድን ነው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ እግዚአብሔር በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር አወጣን፤