ዘፀአት 1:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም፥ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት አድኑአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም፣ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ አባይ ወንዝ ውስጥ ጣሉት፤ ሴት ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት ትኑር” ሲል ሕዝቡን አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም፦ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ዓባይ ወንዝ ጣሉት፥ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት እንድትኖር ተዉአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ንጉሡ “ከዕብራውያን የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ እያነሣችሁ ዓባይ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፤ ሴቶች ልጆች ግን በሕይወት ይኑሩ” ሲል ለሕዝቡ ጥብቅ ትእዛዝ አስተላለፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም፦ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት አድኑአት፤” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ። |
“እናንተ ዕብራውያትን ሴቶች ስታዋልዱ ለመውለድ እንደ ደረሱ በአያችሁ ጊዜ፥ ወንድ ቢሆን ግደሉት፤ ሴት ብትሆን ግን አትግደሏት።”
ሣጥኑን በከፈተችም ጊዜ ሕፃኑን አየች፤ እነሆም፥ ሕፃኑ በሣጥኑ ውስጥ ያለቅስ ነበር፤ የፈርዖንም ልጅ አዘነችለት፥ “ይህ ሕፃን ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው” አለች።
ሙሴ በተወለደ ጊዜ በእምነት ሦስት ወር በአባቱ ቤት ሸሸጉት፤ ሕፃኑ መልካም እንደ ሆነ አይተውታልና፤ የንጉሥንም ትእዛዝ አልፈሩም።