ዘፀአት 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እናንተ ዕብራውያትን ሴቶች ስታዋልዱ ለመውለድ እንደ ደረሱ በአያችሁ ጊዜ፥ ወንድ ቢሆን ግደሉት፤ ሴት ብትሆን ግን አትግደሏት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የዕብራውያንን ሴቶች በማማጫው ድንጋይ ላይ በምታዋልዱበት ጊዜ የሚወለደው ሕፃን ወንድ ከሆነ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የዕብራውያንን ሴቶች ስታዋልዱ፥ ለመውለድ እንደ ደረሱ ባያችሁ ጊዜ፥ ወንድ ከሆነ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የዕብራውያንን ሴቶች በምታዋልዱበት ጊዜ የሚወለደው ሕፃን ወንድ ከሆነ ወዲያውኑ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት እንድትኖር ተዉአት”። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “እናንተ የዕብራያንን ሴቶች ስታዋልዱ፥ ለመውለድ እንደደረሱ ባያችሁ ጊዜ፥ ወንድ ቢሆን ግደሉት፤ ሴት ብትሆን ግን በሕይወት ትኑር።” |
ፈርዖንም፥ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት አድኑአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
ሙሴ በተወለደ ጊዜ በእምነት ሦስት ወር በአባቱ ቤት ሸሸጉት፤ ሕፃኑ መልካም እንደ ሆነ አይተውታልና፤ የንጉሥንም ትእዛዝ አልፈሩም።
ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።