ዘፀአት 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአባታቸው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፤ ሰው ሁሉ ከቤተ ሰቡ ጋር ገባ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤተ ሰቦቻቸውን ይዘው ከያዕቆብ ጋራ ወደ ግብጽ የሄዱት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ገቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የገቡት፥ እስራኤል ተብሎ የተጠራው የያዕቆብ ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፤ ሰው ሁሉ ከቤተ ሰቡ ጋር ገባ። |
ከዚያም በኋላ ነፍስዋ ልትወጣ ደረሰች፤ ሞትዋ በእርሱ ሆኖአልና ስሙን የጭንቀቴ ልጅ ብላ ጠራችው ፤ አባቱ ግን ብንያም አለው።
“የነገዶችም ስም ይህ ነው። በሔትሎን መንገድ አጠገብ ወደ ሐማት መግቢያ፥ በደማስቆም ድንበር በአለው በሐጸርዔናን በሐማትም አጠገብ በሰሜን በኩል ይጀምራል። ድንበራቸውም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። ለዳን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።