ኤፌሶን 1:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህችውም አካሉ ናት፤ የሁሉም ፍጻሜው እርሱ ነው፤ ሁሉንም በሁሉ ይፈጽማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ሁሉን ነገር በሁሉም ረገድ የሚሞላው፣ የርሱ ሙላት የሆነች አካሉ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት፤ ክርስቶስም በቤተ ክርስቲያንና በሌላውም ሁሉ የመላ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት። |
ብዙ ልዩ ልዩ የሆነች የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤
ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ አንድ እስክንሆን ድረስ በክርስቶስ ምልዐት መጠን፥ አካለ መጠን እንደ አደረሰ እንደ አንድ ሙሉ ሰው እስክንሆን ድረስ፥
አሁንም በመከራዬ ደስ ይለኛል፤ አካሉ ስለ ሆነች ስለ ቤተ ክርስቲያን፥ ከክርስቶስ መከራ ጥቂቱን በሥጋዬ እፈጽማለሁ።
ሥጋ ሁሉ ጸንቶ በሚኖርበት፥ በሥርና በጅማትም በሚስማማበት፥ በእግዚአብሔርም በሚያድግበትና በሚጸናበት፥ በሚሞላበትም በራስ አይጸናም።
በእርሱ ዘንድ አይሁዳዊ፥ ግሪካዊም፥ የተገዘረ፥ ያልተገዘረም፥ አረመኔም፥ ባላገርም፥ ቤተ ሰብእና አሳዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክርስቶስ ለሁሉ በሁሉም ዘንድ ነው።