Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤፌሶን 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ፍቅር ለመ​ረ​ዳት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍጹ​ም​ነት በሁሉ ፍጹ​ማን ትሆኑ ዘንድ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እስከ እግዚአብሔር ሙላት ሁሉ ልክ ደርሳችሁ እንድትሞሉ፣ ከመታወቅ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር ታውቁም ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ድረስ እንድትሞሉ፥ እውቀትን የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር እንድታውቁ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ይህን ከሰው ዕውቀት በላይ የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር እንድታውቁ በእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ለመሞላትም እንድትበቁ እጸልያለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 3:19
24 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ ከተ​ግ​ሣ​ጽህ፥ ከመ​ዓ​ት​ህም መን​ፈስ እስ​ት​ን​ፋስ የተ​ነሣ፥ የው​ኆች ምን​ጮች ታዩ፥ የዓ​ለም መሠ​ረ​ቶ​ችም ተገ​ለጡ።


አም​ላ​ኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤ ለያ​ዕ​ቆብ መድ​ኀ​ኒ​ትን ያዘ​ዝህ።


ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ይጠግባሉና።


እኛም ሁላ​ችን ከሙ​ላቱ በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀ​በ​ልን።


ብቻ​ህን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ የሆ​ንህ አን​ተን፥ የላ​ክ​ኸ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ናት።


ከክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ማን ይለ​የ​ናል? መከራ ነውን? ኀዘን ነውን? ስደት ነውን? ራብ ነውን? መራ​ቆት ነውን? ጭን​ቀት ነውን? ሾተል ነውን?


ኀይ​ልም ቢሆን፥ ከፍ​ታም ቢሆን፥ ዝቅ​ታም ቢሆን፥ ሌላ ፍጥ​ረ​ትም ቢሆን ከክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ሊለ​የን የሚ​ችል የለም።


የክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር በዚህ አሳብ እን​ድ​ን​ጸና ያስ​ገ​ድ​ደ​ናል፤ ሁሉ ፈጽ​መው ስለ ሞቱ አንዱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞቶ​አ​ልና።


ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋርም ተሰ​ቀ​ልሁ፤ ሕይ​ወ​ቴም አለ​ቀች፤ ነገር ግን በክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወት አለሁ፤ ዛሬም በሥ​ጋዬ የም​ኖ​ረ​ውን ኑሮ የወ​ደ​ደ​ኝን ስለ እኔም ራሱን አሳ​ልፎ የሰ​ጠ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ በማ​መን እኖ​ራ​ለሁ።


ይህ​ች​ውም አካሉ ናት፤ የሁ​ሉም ፍጻ​ሜው እርሱ ነው፤ ሁሉ​ንም በሁሉ ይፈ​ጽ​ማል።


ስፋ​ቱና ርዝ​መቱ፥ ምጥ​ቀ​ቱና ጥል​ቀቱ ምን ያህል እንደ ሆነ ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ጋር ለማ​ስ​ተ​ዋል ትችሉ ዘንድ፥


ክር​ስ​ቶስ እንደ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ራሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ የሚ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ቍር​ባን አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላ​ችሁ በፍ​ቅር ተመ​ላ​ለሱ።


ወን​ዶ​ችም ክር​ስ​ቶስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንን እንደ ወደ​ዳት፥ ራሱ​ንም ስለ እር​ስዋ ቤዛ አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላት ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይው​ደዱ።


ስለ እና​ንተ ይህን ላስብ ይገ​ባ​ኛል፤ በም​ታ​ሰ​ር​በ​ትና በም​ከ​ራ​ከ​ር​በት፥ ወን​ጌ​ል​ንም በማ​ስ​ተ​ም​ር​በት ጊዜ ከእኔ ጋራ በጸጋ ስለ ተባ​በ​ራ​ችሁ በልቤ ውስጥ ናች​ሁና።


ሁሉ የሚ​ገ​ኝ​ባት፥ ከል​ቡ​ናና ከአ​ሳብ ሁሉ በላይ የም​ት​ሆን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ልባ​ች​ሁ​ንና አሳ​ባ​ች​ሁን ታጽ​ናው።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ገ​ባ​ችሁ ትሄዱ ዘንድ፥ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያ​ፈ​ራ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በማ​ወቅ እያ​ደ​ጋ​ችሁ፥ በሁሉ ደስ ታሰ​ኙት ዘንድ።


እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።


ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos