ኤፌሶን 1:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክርስቶስ እንደ አደረገው እንደ ከሃሊነቱ ታላቅነት በምናምን በእኛ ላይ የሚያደርገው የከሃሊነቱ ጽናት ብዛት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእኛ ለምናምነውም ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነውን ኀይሉን እንድታውቁ እጸልያለሁ። ይህም ኀይል እንደ እርሱ ታላቅ ብርታት አሠራር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእኛ ለምናምነውም ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነውን፥ የኀይሉ ታላቅ ብርታት አሠራር፥ ኀይሉን ምን እንደሆን እንድታውቁ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የማይለካው ታላቅ ኀይሉ ለእኛ ለምናምነው ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ታውቁ ዘንድ እጸልያለሁ፤ ይህንንም ታላቅ ኀይሉን በተግባር ያሳየው ከሞት አስነሥቶ በሰማይ በቀኙ ባስቀመጠው በክርስቶስ አማካይነት ነው። |
ይኸውም ዐይናቸውን ትከፍትላቸው ዘንድ፥ ከጨለማም ወደ ብርሃን፥ ሰይጣንን ከማምለክም ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸው ዘንድ፥ ኀጢአታቸውም ይሰረይላቸው ዘንድ፥ በስሜም በማመን ከቅዱሳን ጋር አንድነትን ያገኙ ዘንድ ነው።’
ወንጌልን ለማስተማር አላፍርምና፤ አስቀድሞ አይሁዳዊን፥ ደግሞም አረማዊን፥ የሚያምኑበትን ሁሉ የሚያድናቸው የእግዚአብሔር ኀይሉ ነውና።
በከሃሊነቱ እንደ ረዳን መጠን፥ የምናስበውንና የምንለምነውን ሁሉ ትሠሩ ዘንድ፥ ታበዙም ዘንድ ሊያጸናችሁ ለሚችል፥
እርሱም እንደ ከሃሊነቱ ረዳትነት መጠን የተዋረደውን ሥጋችንን የሚያድሰው፥ ክቡር ሥጋዉንም እንዲመስል የሚያደርገው፥ የሚያስመስለውም፥ ሁሉም የሚገዛለት ነው።
በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችኋል፤ በእርስዋም ከሙታን ለይቶ ባስነሣው በእግዚአብሔር ረዳትነትና በሃይማኖት ከእርሱ ጋር ተነሥታችኋል።
ወንጌላችን በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።
ስለዚህም ደግሞ እንደ አምላካችን እንደ ጌታም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር እናንተም በእርሱ ዘንድ ልትከብሩ፥ አምላካችን ለመጥራቱ የምትበቁ አድርጎ ይቈጥራችሁ ዘንድ፥ የበጎነትንም ፈቃድ ሁሉ የእምነትንም ሥራ በኀይል ይፈጽም ዘንድ ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን።
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።