መክብብ 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉን ከሚያደርጉ ወገን ፈጥኖ ክርክርን የሚያደርግ የለምና፤ ስለዚህ የሰው ልጆች ልብ በእነርሱ ክፉን ለመሥራት ጠነከረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በወንጀል ላይ ባፋጣኝ ፍርድ ካልተሰጠ፣ የሰዎች ልብ ክፉን በማድረግ ዕቅድ ይሞላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክፉ ሥራ ላይ ፈጥኖ ፍርድ አይበየንምና በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ክፉን መሥራት ጠነከረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ሆን ብለው ወንጀል የሚሠሩት ለምንድን ነው? የዚህ ምክንያት ሌላ ሳይሆን ወንጀል በሚሠሩ ሰዎች ላይ ፈጣን የቅጣት ፍርድ ባለመሰጠቱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክፉ ሥራ ላይ ፈጥኖ ፍርድ አይፈረድምና ስለዚህ በሰው ልጆች ውስጥ ልባቸው ክፉን ለመሥራት ጠነከረ። |
እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ ዐይኖቹም ወደ ድሃ ይመለከታሉ፤ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
ከፀሓይ በታች የተደረገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋትን ትሞላለች፥ በሕይወታቸው ሳሉ ሁከት በልባቸው አለ፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።
በምድር ጽድቅን የማይማርና መልካምን የማያደርግ ኃጥእ አልቆአልና፥ የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ኀጢአተኛን ያስወግዱታል።
ሐሰት የተናገርሽው፥ እኔንም ያላሰብሽው፥ በልብሽም ነገሩን ያላኖርሽው ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔም ዝም አልሁሽ፤ አንቺም አልፈራሽኝም።
ስለዚህ እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ! አሁን እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ግብፅም ትገቡ ዘንድ በዚያም ትቀመጡ ዘንድ ፊታችሁን ብታቀኑ፤
“ሞአብ ከልጅነቷ ጀምራ ዐረፈች፤ በክብርዋም ቅምጥል ነበረች፤ ወይንዋም ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ ወደ ምርኮም አልሄደችም፤ ስለዚህ ቃናው በእርስዋ ውስጥ ቀርቶአል፤ መዓዛዋም አልተለወጠም።