መክብብ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኩል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአፍህ አትፍጠን፤ በአምላክም ፊት ማንኛውንም ነገር ለመናገር፣ በልብህ አትቸኵል፤ አምላክ በሰማይ፣ አንተ ደግሞ በምድር ነህ፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል፥ እንዲሁም የአላዋቂም ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመናገርህ በፊት አስብ፤ ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ለመስጠት በችኰላ ስእለት አታድርግ፤ እግዚአብሔር በሰማይ አንተ ግን በምድር መሆንህን በማሰብ የምትናገረው ቃል የተመጠነ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል፥ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን። |
አብርሃምም እንደገና ነገሩን ደገመ፤ እንዲህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ሠላሳው አላጠፋትም” አለው።
አብርሃምም አለው፥ “አቤቱ እንደገና እናገር ዘንድ ፍቀድልኝ፤ ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ዐሥሩ አላጠፋትም” አለው።
ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፥ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ፥ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
ለሐውልት ያቆምኋት ይህችም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ትሆንልኛለች፤ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከዐሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።”
ሰው ሳያስብ ክፉን ወይም መልካምን ያደርግ ዘንድ ሳያስብ በከንፈሩ ተናግሮ ቢምል፥ ሳያስብ የማለውም ከዚህ ባንዱ ነገር ቢሆን፥ በታወቀው ጊዜ ከዚህ ነገር በአንዱ በደለኛ ይሆናል።