መክብብ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነዚህም ከሁለቱ ይልቅ ገና ያልተወለደው ከፀሓይም በታች የሚደረገውን ክፉ ሥራ ሁሉ ያላየ ይሻላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ከሁለቱም ይልቅ፣ ገና ያልተወለደው፣ ከፀሓይ በታች የሚደረገውንም፣ ክፋት ያላየው ይሻላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነዚህም ከሁለቱ ይልቅ ገና ያልተወለደው ከፀሐይም በታች የሚደረገውን ግፍ ያላየው ይሻላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተለይም ከነዚህ ከሁለቱ ወገኖች ይልቅ ከቶውኑ ያልተወለዱና በዚህ ዓለም የሚፈጸመውን ግፍና ጭቈና ያላዩ ዕድለኞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነዚህም ከሁለቱ ይልቅ ገና ያልተወለደው ከፀሐይም በታች የሚደረገውን ግፍ ያላየው ይሻላል። |