ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት በድካሙም ለሰውነቱ መልካም ነገር ከሚያሳያት በቀር በጎ ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ።
መክብብ 2:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያለ እርሱ ፈቃድ የሚበላ ወይም የሚጠጣ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ዘንድ ካልሆነ ማን መብላትና መደሰት ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያለ እርሱ ፈቃድ ማን ይበላል፥ ማንስ ተድላን ይቀምሳል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለ እርሱ ፈቃድማ እየበላና እየጠጣ ተድላ ደስታ ማድረግ የሚችል ማን አለ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያለ እርሱ ፈቃድ የበላ ደስ ብሎትም ተድላን የቀመሰ ማን ነው? |
ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት በድካሙም ለሰውነቱ መልካም ነገር ከሚያሳያት በቀር በጎ ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ።
እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበብንና ዕውቀትን፥ ደስታንም ይሰጠዋል፤ ለኀጢአተኛ ግን በእግዚአብሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።