La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መክብብ 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም ብር​ሃን ከጨ​ለማ እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ እን​ዲሁ ከአ​ላ​ዋቂ ይልቅ ለብ​ልህ ብልጫ እን​ዳ​ለው ተመ​ለ​ከ​ትሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ብርሃን ከጨለማ እንደሚበልጥ ሁሉ፣ ጥበብም ከሞኝነት እንደሚበልጥ ተመለከትሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔ ብርሃን ከጨለማ እንደሚበልጥ እንዲሁ ጥበብ ከአለማወቅ እንደሚበልጥ አየሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲህም አልኩ “በእርግጥ ብርሃን ከጨለማ እንደሚሻል ጥበብም ከሞኝነት መሻልዋን ተመለከትኩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔ ብርሃን ከጨለማ እንደሚበልጥ እንዲሁ ጥበብ ከስንፍና እንዲበልጥ አየሁ።

Ver Capítulo



መክብብ 2:13
17 Referencias Cruzadas  

የዐዋቂዎች ጥበብ መንገዳቸውን ታውቃለች፤ የሰነፎች ስንፍና ግን ወደ ስሕተት ይመራል።


ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ከወርቅ ይመረጣል። ዕውቀትንም ገንዘብ ማድረግ ከብር ይሻላል።


ምሣሩ ከዛ​ቢ​ያው ቢወ​ልቅ ሰው​የው ፊቱን ወዲ​ያና ወዲህ ይላል፤ ብዙ ኀይ​ልም ያስ​ፈ​ል​ገ​ዋል። ጥበብ ግን ለብ​ርቱ ሰው ትርፉ ነው፤


ብር​ሃን ጣፋጭ ነው፥ ፀሓ​ይ​ንም ማየት ለዐ​ይን መል​ካም ነው።


በከ​ተማ ከሚ​ኖሩ ዐሥር ገዢ​ዎች ይልቅ ጥበብ ጠቢ​ብን ትረ​ዳ​ዋ​ለች።


እኔም፥ “ከኀ​ይል ይልቅ ጥበብ ትበ​ል​ጣ​ለች፤ የድ​ሃው ጥበብ ግን ተና​ቀች ቃሉም አል​ተ​ሰ​ማ​ችም” አልሁ።


ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎች ይልቅ ጥበብ ትሻ​ላ​ለች፤ አንድ ኀጢ​አ​ተኛ ግን ብዙ መል​ካ​ምን ያጠ​ፋል።


ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ ለእግዚአብሔር በሚገዛውና በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ።


ዐይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!


ቀድሞ ጨለማ ነበ​ራ​ች​ሁና፥ ዛሬ ግን በጌ​ታ​ችን ብር​ሃን ሆና​ች​ኋል። እን​ግ​ዲ​ህስ እንደ ብር​ሃን ልጆች ተመ​ላ​ለሱ።