ዘዳግም 6:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ዛሬም በሕይወት እንዲያኖረን፥ ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን፥ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፈራ ዘንድ፥ ይህችንም ሥርዐት ሁሉ እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ምን ጊዜም መልካም እንዲሆንልንና በሕይወት እንድንኖር ይህን ሥርዐት ሁሉ እንድንፈጽም፣ አምላካችንንም እግዚአብሔርን እንድንፈራ እግዚአብሔር አዘዘን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬም በሕይወት እንዳኖረን፥ ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን፥ አምላካችንን ጌታን እንድንፈራ፥ እነዚህንም ሥርዓቶች ሁሉ እንድንፈጽም ጌታ አዘዘን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር አምላካችን እነዚህን ደንቦች እንድንፈጽምና እርሱንም እንድንፈራው አዞናል፤ እኛም ይህን ብናደርግ እርሱ ዘወትር ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ እንዲከናወንልን ያደርጋል፤ ዛሬ እንደሚያደርገውም ሁሉ በሕይወት ያኖረናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ዛሬም በሕይወት እንዲያኖረን፥ ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን፥ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፈራ ዘንድ፥ ይህችንም ሥርዓት ሁሉ እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘን። |
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ፥ ኀጢአትንም እንዳትሠሩ እርሱን መፍራት በእናንተ ያድር ዘንድ መጥቶአልና አትፍሩ” አላቸው።
ልጄ ሆይ፥ ለራስህ ጠቢብ ብትሆን ለባልንጀራህም ጠቢብ ትሆናለህ፥ ክፉም ብትሆን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚያዘጋጅ ሰው ይመስላል። እርሱም የሚበርር ዎፍን እንደሚከተል ነው። የወይኑ ቦታ መንገዱን ተወ፤ የሚሰማራባትን መንገድ ዘነጋ፤ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች ምድርም ይሄዳል፤ የማያፈራና የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።
ክፉ ምክርን መክረዋልና ለነፍሳቸው ወዮላት! እንዲህም አሉ፥ “ጻድቁን እንሻረው፤ ሸክም ሆኖብናልና፤” ስለዚህ የእጃቸውን ሥራ ፍሬ ይበላሉ።
ለእነርሱም፥ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘለዓለም እንዲፈሩኝ ሌላ መንገድና ሌላ ልብ እሰጣቸዋለሁ።
“አሁንም እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወትም እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ ዛሬ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።
እናንተ፥ ልጆቻችሁም፥ የልጅ ልጆቻችሁም በዕድሜአችሁ ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ፈርታችሁ እኔ ለእናንተ ያዘዝሁትን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ፥ ዕድሜአችሁም ይረዝም ዘንድ፤
“በሕይወት እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱአት፥ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ።
ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፤ አንተም ያላወቅኸውን፥ አባቶችህም ያላወቁትን መና መገበህ።