La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 6:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብ​ፅና በፈ​ር​ዖን በቤ​ቱም ሁሉ ላይ በፊ​ታ​ችን ታላ​ቅና ክፉ ምል​ክት፥ ተአ​ም​ራ​ትም አደ​ረገ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኛ በዐይናችን እያየን እግዚአብሔር ታላላቅና አስፈሪ የሆኑ ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆችን በግብጽ፣ በፈርዖንና በመላው ቤተ ሰዎቹ ላይ አደረገ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም በግብጽና በፈርዖን በቤቱም ሁሉ ላይ፥ በዓይናችን እያየን፥ ታላቅና አሰቃቂ፥ ምልክት ተአምራትም አደረገ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ግብጻውያንን፥ ንጉሣቸውንና መኰንኖቻቸውን በብርቱ የሚጐዱ ታላላቅ ተአምራትን ማድረጉን በገዛ ዐይኖቻችን ዐይተናል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም በግብፅና በፈርዖን በቤቱም ሁሉ ላይ እኛ እያየን ታላቅና ክፋ ምልክት ተአምራትም አደረገ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 6:22
15 Referencias Cruzadas  

ለጨ​ረ​ቃና ለከ​ዋ​ክ​ብት ሌሊ​ትን ያስ​ገ​ዛ​ቸው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዝማሬ በባ​ዕድ ምድር እን​ዴት እን​ዘ​ም​ራ​ለን?


አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ልዑል ነህ፤


በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ላይ የተ​ዘ​ባ​በ​ት​ሁ​ትን ሁሉ፥ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ቸ​ው​ንም ተአ​ም​ራ​ቴን በል​ጆ​ቻ​ች​ሁና በልጅ ልጆ​ቻ​ችሁ ጆሮች ትነ​ግሩ ዘንድ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”


እኔም እጄን እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ በማ​ደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ውም ተአ​ም​ራቴ ሁሉ ግብ​ፅን እመ​ታ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይለ​ቅ​ቋ​ች​ኋል።


በፊ​ታ​ችሁ የሚ​ሄ​ደው አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በግ​ብፅ ምድር እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ ሁሉ፥ ስለ እና​ንተ አብ​ሮ​አ​ችሁ ይዋ​ጋል፤


በዚ​ያም ጊዜ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ሁት፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ ነገ​ሥት ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ዐይ​ኖ​ችህ አይ​ተ​ዋል፤ እን​ዲሁ በም​ታ​ል​ፍ​ባ​ቸው መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋል።


ብዔ​ል​ፌ​ጎ​ርን የተ​ከ​ተ​ለ​ውን ሰው ሁሉ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ለይቶ አጥ​ፍ​ቶ​ታ​ልና አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ዔ​ል​ፌ​ጎር ያደ​ረ​ገ​ውን ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ አይ​ተ​ዋል።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በግ​ብፅ ለእ​ና​ንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈ​ተ​ናና በተ​አ​ም​ራት፥ በድ​ን​ቅና በሰ​ልፍ፥ በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ማስ​ፈ​ራ​ራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሌላ ሕዝብ መካ​ከል ገብቶ ለእ​ርሱ ሕዝ​ብን ይወ​ስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥


አንተ ልጅ​ህን በለው፦ በግ​ብፅ የፈ​ር​ዖን ባሪ​ያ​ዎች ነበ​ርን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጽኑ እጅ፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ከዚያ አወ​ጣን፤


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ንና እር​ስ​ዋን ይሰ​ጠን ዘንድ እኛን ከዚያ አወ​ጣን።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓይ​ንህ እያ​የች፥ ታላቅ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ ምል​ክ​ት​ንም፥ ተአ​ም​ራ​ት​ንም፥ የጸ​ና​ች​ው​ንም እጅ፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ው​ንም ክንድ አድ​ርጎ እን​ዳ​ወ​ጣህ፤ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ያደ​ር​ጋል።