እግዚአብሔር ሙሴን አለው፥ “ለያዕቆብ ቤት ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ በል፦ እኔ ከሰማይ እንደ ተናገርኋችሁ እናንተ አይታችኋል።
ዘዳግም 4:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ከእሳት መካከል ሆኖ ሲናገር የሕያው እግዚአብሔርን ድምፅ እንደ ሰማህና በሕይወት እንዳለህ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ እንደ ሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእሳት ውስጥ የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደ እናንተ የሰማና በሕይወት የኖረ ከቶ ሌላ ሕዝብ አለን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተን ከእሳት ውስጥ ሆኖ እንደ ተናገረው፥ የእግዚአብሔርን ድምፅ ሰምቶ በሕይወት መኖር የቻለ፥ ሌላ ሕዝብ ከቶ አለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በሰማችሁት ዐይነት እግዚአብሔር በእሳት ነበልባል ውስጥ ሆኖ ተናግሮት በሕይወት ለመኖር የቻለ ሕዝብ ከቶ አለን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ከእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደ ሰማህ፥ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ በሕይወት ይኖራልን? |
እግዚአብሔር ሙሴን አለው፥ “ለያዕቆብ ቤት ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ በል፦ እኔ ከሰማይ እንደ ተናገርኋችሁ እናንተ አይታችኋል።
“እግዚአብሔር በተራራው ላይ፤ በእሳትና በጨለማ፥ በጭጋግና በዓውሎ ነፋስ መካከል ሆኖ በታላቅ ድምፅ እነዚህን ቃሎች ለጉባኤያችሁ ሁሉ ተናገረ፤ ምንም አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላት ላይ ጻፋቸው፤ ለእኔም ሰጣቸው።
አላችሁም፦ እነሆ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፤ ከእሳቱም መካከል ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰው ጋር ሲነጋገር፥ ሰውዬው በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል።
እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉትን ሁለት የድንጋይ ጽላት ሰጠኝ፤ በተሰበሰባችሁ ጊዜ እግዚአብሔር በተራራው ላይ የነገረኝ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር።
ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ ዐወቀ። ጌዴዎንም፥ “አቤቱ! አምላኬ ሆይ! ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና” አለ።