ዘዳግም 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፤ ተራራውም እስከ ሰማይ ድረስ በእሳት ይነድድ ነበር፤ ጨለማና አውሎ ነፋስ፥ ድቅድቅ ጨለማም ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተራራው በጥቍር ደመናና በድቅድቅ ጨለማ ተውጦ ሳለ ነበልባሉ ሰማይ እስከሚደርስ ድረስ በተቃጠለ ጊዜ መጥታችሁ ከተራራው ግርጌ ቆማችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፥ እስከ ሰማይም ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፥ ጨለማም ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስከ ሰማይ በሚደርስ የእሳት ነበልባልና ጥቅጥቅ ባለ የጢስ ደመና ወደተጋረደው ተራራ ግርጌ ቀርባችሁ ቆማችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፤ እስከ ሰማይም መካከል ድረስ አሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፤ ጨለማና ደመና ድቅድቅ ጨለማም ነበረ። |
ከምድር መናወጥ በኋላ እሳት ሆነ፤ እግዚአብሔርም በእሳቱ ውስጥ አልነበረም። ከእሳቱም በኋላ እንደ ፉጨት ያለ ቀጭን ድምፅ ሆነ፤ በዚያም እግዚአብሔር ነበረ።
እግዚአብሔር ሙሴን፥ “ከአንተ ጋር ስነጋገር ሕዝቡ እንዲሰሙ፥ ደግሞም ለዘለዓለም እንዲያምኑብህ፥ እነሆ፥ በዐምደ ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ” አለው። ሙሴም የሕዝቡን ቃል ለእግዚአብሔር ነገረ።
“እንዲህም ሆነ፤ በእሳት መካከል ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ፥ ተራራውም በእሳት ሲነድድ እናንተ፥ የነገዶቻችሁ አለቆች፥ ሽማግሌዎቻችሁም፥ ወደ እኔ ቀረባችሁ፤