እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ግርማ፥ በታላቅ ተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን፤
ዘዳግም 34:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤል ሁሉ ፊት በታላቅ ተአምር ሁሉና በጸናች እጅ፥ በተዘረጋችም ክንድ ሁሉ እንዳደረገው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ አልተነሣም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ በእስራኤል ሁሉ ፊት ያሳየውን ታላቅ ኀይል ያሳየ ወይም ያደረገውን አስፈሪ ተግባር የፈጸመ ማንም ሰው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሙሴ በእስራኤል ሁሉ ፊት ያሳየውን የጸና ክንድ ያሳየ ወይም ያደረገውን አስፈሪ ነገር የፈጸመ ማንም የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት ያደረገውን ዐይነት ታላቅና አስፈሪ ነገር ሁሉ ያደረገ ሌላ ነቢይ ከቶ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤል ሁሉ ፊት በጸናች እጅ ሁሉና በታላቅ ማስደንገጥ ሁሉ እንዳደረገው እንደ ሙሴ ያለ አልተነሣም። |
እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ግርማ፥ በታላቅ ተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን፤
በግብፅ ምድር በፈርዖንና በሹሞቹ ሁሉ ላይ፥ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ምልክትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ላከው ያለ፥
አምላካችን እግዚአብሔር በዐይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈተናና በተአምራት፥ በድንቅና በሰልፍ፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ማስፈራራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ገብቶ ለእርሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥
እንዲህም ሆነ፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦