La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 32:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምድር በዓ​ባ​ሪም ተራራ ውስጥ ወዳ​ለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ርስት አድ​ርጌ የም​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እያት፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር፣ ከዓባሪም ተራሮች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ናባው ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር፥ ከዓባሪም ተራራዎች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ነቦ ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“በሞአብ ምድር በኢያሪኮ ከተማ ፊት ለፊት ወደሚገኙት የዐባሪም ተራራዎች ሂድ፤ ወደ ነቦ ተራራም ውጣ፤ ከዚያም ለእስራኤል ሕዝብ የማወርሳትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደዚህ በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ምድር በዓባሪም ተራራ ውስጥ ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች ርስት አድርጌ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እይ፤

Ver Capítulo



ዘዳግም 32:49
10 Referencias Cruzadas  

በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ር​ባ​ትን ይህ​ችን ምድር፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ሁሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​አት ዘንድ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”


ንጉ​ሥን በክ​ብሩ ታዩ​ታ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በሩቅ ያለች ምድ​ርን ያዩ​አ​ታል።


ወዳ​ጆ​ችሽ ሁሉ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና ወደ ሊባ​ኖስ ወጥ​ተሽ ጩኺ፤ በባ​ሳ​ንም ላይ ድም​ፅ​ሽን አንሺ፤ በባ​ሕ​ሩም ማዶ ጩኺ።


“ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ እኔ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ርስት ወደ ከነ​ዓን ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ እኔም የለ​ምጽ ደዌ ምል​ክት በር​ስ​ታ​ችሁ ምድር ቤቶች ባደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ​ዚህ በና​ባው አሻ​ገር ወዳ​ለው ተራራ ውጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ይገ​ዙ​አት ዘንድ እኔ የም​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እያት፤


ኢያ​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም በተራ ተቀ​ብ​ለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ፊት አስ​ወ​ጥቶ ወደ ሰደ​ዳ​ቸው ወደ አሕ​ዛብ ሀገር ከእ​ነ​ርሱ ጋር አገ​ቡ​አት፤ እስከ ዳዊት ዘመ​ንም ነበ​ረች።


በም​ድር ያለው ማደ​ሪያ ቤታ​ችን ቢፈ​ር​ስም፥ በሰ​ማይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰው እጅ ያል​ሠ​ራው ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ቤት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን።


ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ር​ምና ወደ ተራ​ራው ራስ ውጣ፤ ዐይ​ን​ህ​ንም ወደ ባሕር ወደ መስ​ዕም፥ ወደ አዜ​ብም ወደ ምሥ​ራ​ቅም አን​ሥ​ተህ በዐ​ይ​ንህ ተመ​ል​ከት።