እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፤ በእርሱም እታመናለሁ፤ ጋሻዬና የመድኀኒቴ ቀንድ፥ ረዳቴ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኀኒቴ ሆይ፥ ከግፈኛ ታድነኛለህ።
ዘዳግም 32:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አለ፦ ትታመኑባቸው የነበሩት አማልክት የት አሉ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም ይላል፤ “መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፣ እነዚያ አማልክታቸው የት አሉ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ሕዝቡን እንዲህ ይላል፦ ‘ይታመኑባቸው የነበሩት አምባዎች፥ አማልክቶቻቸው የት ናቸው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ሕዝቡን እንዲህ ብሎ ጠየቀ፦ ‘የሚተማመኑባቸው አማልክቶቻቸው የት አሉ? ከዚያም የተማመኑበት አለት አማልክቶቻቸውስ የት አሉ’ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ይላል፦ አማልክቶቻቸው የት ናቸው? 2 ይታመኑባቸው የነበሩት አማልክት? |
እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፤ በእርሱም እታመናለሁ፤ ጋሻዬና የመድኀኒቴ ቀንድ፥ ረዳቴ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኀኒቴ ሆይ፥ ከግፈኛ ታድነኛለህ።
ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ፥ “እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባትህ ነቢያትና ወደ እናትህ ነቢያት ሂድ፥” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ፥ “አይደለም፤ በሞዓብ እጅ ይጥላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እነዚህን ሦስት ነገሥታት ጠርቶአልን?” አለው።
በዚያች ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ፥ እነርሱ አምላኮቻቸውን ተከትለው በአመነዘሩና በሠዉላቸው ጊዜ እንዳይጠሩህ፥ ከመሥዋዕታቸውም እንዳትበላ፥
ዓለትም ትውጣቸዋለች ድልም ይሆናሉ የሸሸም ይያዛል። በጽዮን ዘርእ፥ በኢየሩሳሌምም ቤቶች ያሉት ብፁዕ ነው” ይላል እግዚአብሔር።
በይሁዳም ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሄደው ወደሚያጥኑላቸው፥ በመከራቸው ጊዜ ከቶ ወደማያድኗቸው አማልክት ይጮኻሉ።
ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ግን ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ፤ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ። በኢየሩሳሌምም በመንገዶችዋ ቍጥር ለጣዖት ሠዉ።
የባቢሎን ንጉሥ በእናንተና በዚህች ሀገር አይመጣባችሁም ብለው ትንቢት ይናገሩላችሁ የነበሩ ነቢያቶቻችሁ ወዴት አሉ?