ዘዳግም 32:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወይን ጠጃቸው የእባብ መርዝ፥ የሚገድልም የእፉኝት መርዝ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይናቸው የእባብ መርዝ፣ የመራዥ እባብም መርዝ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይናቸው የእባብ መርዝ፥ የጨካኝ እፉኝት መርዝ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይናቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤ እንደ ክፉ እፉኝትም መርዝ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወይን ጠጃቸው የእባብ መርዝ፥ 2 የእፉኝትም ሥራይ ነው። |
አንተም አቤቱ፥ የኀያላን አምላክ፥ የእስራኤል ንጉሥ፥ አሕዛብን ሁሉ ጐብኛቸው፥ ይቅርም በላቸው፤ ዐመፅ የሚያደርጉትን ሁሉ ግን አትማራቸው።
“ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።