La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 32:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አይቶ ቀና፤ በወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችም ፈጽሞ ተቈጣ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ይህን አይቶ ናቃቸው፤ በወንድና በሴት ልጆቹ ተቈጥቷልና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ስላስቆጡት ጌታ አይቶ ጣላቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው ስላስቈጡት እግዚአብሔር አስወገዳቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ስላስቈጡት 2 እግዚአብሔር አይቶ ጣላቸው።

Ver Capítulo



ዘዳግም 32:19
18 Referencias Cruzadas  

አንተ የሠ​ራ​ኸ​ውን እነሆ፥ እነ​ርሱ አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፤ ጻድቅ ግን ምን አደ​ረገ?


በአ​ለ​ቆ​ችም ላይ ኀሣር ፈሰሰ፥ መን​ገ​ድም በሌ​ለ​በት በም​ድረ በዳ አሳ​ታ​ቸው።


አንተ በደ​ልን የሚ​ወ​ድድ አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ህ​ምና፤ ክፉ​ዎች ከአ​ንተ ጋር አያ​ድ​ሩም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድ​ርም አድ​ምጪ፤ ልጆ​ችን ወለ​ድሁ፤ አሳ​ደ​ግ​ሁም፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፁ​ብኝ።


ወዳጄ በቤቴ ውስጥ ለምን ርኵ​ሰ​ትን አደ​ረ​ገች? ስእ​ለት ወይም የተ​ቀ​ደሰ ሥጋ ክፋ​ት​ሽን ከአ​ንቺ ያስ​ወ​ግ​ዳ​ልን? ወይስ በእ​ነ​ዚህ ታመ​ል​ጫ​ለ​ሽን?


የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ኤር​ም​ያ​ስን ወሰ​ደው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተና​ገረ።


ዋው። ማደ​ሪ​ያ​ውን እንደ ወይን ጋረደ፤ በዓ​ሉን ሁሉ አጠፋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ያደ​ረ​ገ​ውን በዓ​ሉ​ንና ሰን​በ​ቱን አስ​ረሳ፤ በቍ​ጣ​ውም መዓት ነገ​ሥ​ታ​ቱን፥ አለ​ቆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱን አጠፋ።


ማደ​ሪ​ያ​ዬ​ንም በእ​ና​ንተ መካ​ከል አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም አት​ጸ​የ​ፋ​ች​ሁም።


የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ች​ሁን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ በእጅ የተ​ሠሩ የዕ​ን​ጨት ምስ​ሎ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጠ​ፋ​ለሁ፤ ሬሳ​ች​ሁ​ንም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ሬሳ​ዎች ላይ እጥ​ላ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም ትጸ​የ​ፋ​ች​ኋ​ለች።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “የያ​ዕ​ቆ​ብን ትዕ​ቢት አረ​ክ​ሳ​ለሁ፤ ሀገ​ሮ​ቹ​ንም ጠላሁ፤ ከተ​ሞ​ቹ​ንም ከሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ሰዎች ጋር አጠ​ፋ​ለሁ” ብሎ በራሱ ምሎ​አ​ልና።


በአንድ ወርም ሦስቱን እረኞች አጠፋሁ፣ ነፍሴም ተሰቀቀቻቸው፥ ነፍሳቸውም ደግሞ እኔን ጠላች።


እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተቈጣ፤ ወደ ማረ​ኳ​ቸ​ውም ማራ​ኪ​ዎች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ማረ​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ባሉት በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወዲያ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሊቋ​ቋሙ አል​ቻ​ሉም።