በሬማት ዘገለዓድ የጌቤር ልጅ ነበረ፤ ለእርሱም በገለዓድ ያሉት የምናሴ ልጅ የኢያዕር መንደሮች ነበሩ፤ ለእርሱም ደግሞ በባሳን፥ በአርጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥርና የናስ መወርወሪያዎች የነበረባቸው ስድሳ ታላላቅ ከተሞች ነበሩበት፤
ዘዳግም 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን፤ ከእነርሱም ያልወሰድነው ሀገር የለም፤ በባሳን ያለውን የዐግን መንግሥት፥ የአርጎብን አውራጃዎች ሁሉ፥ ስድሳ ከተሞችን ወሰድን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ የዐግ ግዛት ከሆነው፣ በባሳን ከሚገኘው ከጠቅላላው የአርጎብ ክልል ስድሳ ከተሞች ውስጥ፣ እኛ ያልያዝነው አንድም ከተማ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያን ጊዜም ከተሞቹ ሁሉ ያዝን፥ የአርጎብን ግዛቶች ሁሉ፥ ከሥልሳ ከተሞች ጋር፥ በባሳን ያለውን የዖግን መንግሥት፥ ያልወሰድነው ምንም ከተማ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያኑ ጊዜ ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ ያልወሰድነው ምንም ከተማ አልነበረም፤ በዚህም ዐይነት የባሳን ንጉሥ ዖግ በአርጎብ ግዛት ያስተዳድራቸው የነበሩትን ሥልሳ ከተሞች ወሰድን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን፤ አንድም ያልወሰድነው የለም፤ በባሳን ያለውን የዐግን መንግሥት፥ የአርጎብን አገር ሁሉ፥ ስድሳ ከተሞችን ወሰድን። |
በሬማት ዘገለዓድ የጌቤር ልጅ ነበረ፤ ለእርሱም በገለዓድ ያሉት የምናሴ ልጅ የኢያዕር መንደሮች ነበሩ፤ ለእርሱም ደግሞ በባሳን፥ በአርጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥርና የናስ መወርወሪያዎች የነበረባቸው ስድሳ ታላላቅ ከተሞች ነበሩበት፤
ከገለዐድም የቀረውን የዐግን መንግሥት ባሳንን ሁሉ፥ የአርጎብንም ምድር ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ፤ ያችም ባሳን ሁሉ የራፋይም ሀገር ተብላ ተቈጠረች።
የምናሴ ልጅ ኢያዕር እስከ ጌርጋሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአርጎብን አውራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህችንም የባሳንን ምድር እስከዚች ቀን ድረስ በስሙ አውታይ ኢያዕር ብሎ ጠራ።
አምላካችን እግዚአብሔርም ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዐግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም አጠፋነው፤ አንድ ሰው እንኳን ለዘር አልቀረለትም።
እጅግ ብዙ ከሆኑት ከፌርዜዎን ከተሞች ሌላ፥ እነዚህ ከተሞች ሁሉ ቁመቱ ረዥም በሆነ ቅጥር በመዝጊያና በመወርወሪያም የተመሸጉ ነበሩ።
የእርሱንና የባሳንን ንጉሥ፥ የዐግን ምድር፥ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩትን የሁለቱን የአሞሬዎንን ነገሥታት ምድር ወሰዱ።