ዘዳግም 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም እግዚአብሔር እንደ እናንተ፥ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚያም በኋላ ሁላችሁ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም፣ እግዚአብሔር ለእናንተ እንዳደረገው ሁሉ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፋቸውና አምላካችሁ እግዚአብሔር ከዮርዳኖስ ማዶ የሚሰጣቸውን ምድር እነርሱም እንደዚሁ እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያ በኋላ እያንዳንዳችሁ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይኸውም ጌታ እናንተን እንዳሳረፈ፥ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ ጌታ አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ሁሉ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለእናንተ በዚህ እንዳደረገላችሁ ሁሉ፥ ለእነርሱም ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ በኩል የሚያወርሳቸውን ምድር ሰጥቶ በሰላም እስካሳረፋቸው ድረስ ወገኖቻችሁን እስራኤላውያንን እርዱ፤ ከዚያም በኋላ እኔ ወደ ሰጠኋችሁ ወደዚህች ምድር መመለስ ትችላላችሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይኸውም እግዚአብሔር እናንተን እንዳሳረፈ፥ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ሁሉ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ። |
ምድሪቱም በእግዚአብሔር ፊት ድል እስክትሆን ድረስ ከዚያም በኋላ ትመለሳላችሁ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በእስራኤል ዘንድ ንጹሓን ትሆናላችሁ፤ ይህች ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ርስት ትሆናችኋለች።
በዚያም ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ብዬ አዘዝሁት፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥት ያደረገውን ሁሉ ዐይኖችህ አይተዋል፤ እንዲሁ በምታልፍባቸው መንግሥታት ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያደርጋል።
አምላካችን እግዚአብሔር እንደ እናንተ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ አምላካችን እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ፤ ከዚያም በኋላ ከእናንተ እያንዳንዱ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በፀሐይ መውጫ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ትገባላችሁ፤ ትወርሱአትማላችሁ።”
አሁንም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው ወንድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል፤ አሁን እንግዲህ ተመለሱ፤ ወደ ቤታችሁና የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ።
“በብዙ ብልጥግና፥ በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”
የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ሄዱ፤ በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ በከነዓን ምድር ካለችው ከሴሎ ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ተመለሱ።